ቀጣዮቹ የጦር ፍጥጫዎች በድሮኖች ሊወሰኑ ይችላል?

ቀጣዮቹ የጦር ፍጥጫዎች በድሮኖች ሊወሰኑ ይችላል?
ታትሟል

በጦር ሜዳዎች የበላይ ለመሆን ታንኮችና ተዋጊ ጄቶች ያላቸው ሚና አነስተኛ ሆኗል። ድሮኖች የበለጠ የዘመኑ እና ውጤታማ እየሆኑ ነው። በሚቀጥሉት አምስት ዓመታት በዓለም ላይ ያሉ የትልልቅ ጦር ባለቤቶች አንድ ሚሊዮን፣ 5 ሚሊዮን ወይም 10 ሚሊዮን የድሮን ጦር እየገነቡ መሆኑን መግለጫ ሲሰጡ ማየት የተለመደ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል። ለመሆኑ አዲሱ የድሮኖች አካሄድ ምን ይመስላል?