BBC News, አማርኛ - ዜና
ዜና
በቀይ ባሕር እንቅስቃሴ ላይ ስጋት የፈጠረው እና ሚሊዮኖች የሚጠየቅበት የሶማሊያ ባሕር ላይ ውንብድና
ባለፈው ሳምንት በአራት ቀናት ውስጥ ሁለት የንግድ ጭነት መርከቦች በኤደን ባሕረ ሰላጤ በባሕር ላይ ዘራፊዎች ተይዘዋል። ይህም ከዓመቱ መጀመሪያ አንስቶ የተጠለፉ መርከቦች ቁጥርን ቢያንስ 13 እንዲደርስ አድርጓል። ይህ ክስተት የባሕር ላይ ወንበዴዎችን ለመከላከል እስካሁን ታይቶ የማያውቅ የድሮን ጥቃት እንዲካሄድ ምክንያት ሆኗል።
ቀጥታ, አሜሪካ የሚጠበቅባትን ሳትፈጽም ሆርሙዝ ወሽመጥ እንደማይከፈት ኢራን አስታወቀች
የሆርሙዝ ወሽመጥን በሚመለከት ኢራን እና ኦማን ከመግባባት ላይ መድረሳቸውን፣ ነገር ግን ወሳኙ የባሕር ላይ መተላለፊያ የሚከፈተው አሜሪካ የሚጠበቅባትን ግዴታ ስትወጣ ብቻ መሆኑን የኢራን ባለሥልጣን ተናገሩ። የኢራን ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ካዜም ጋሪባባዲ እንዳስታወቁት የሆርሙዝ ወሽመጥን በሚመለከት በሁለቱ አገራት መካከል በተደረገው ንግግር ለሚተላለፉ መርከቦች ጊዜያዊ የጉዞ መስመር በመክፈት ላይ ከመግባባት መደረሱን ገለጹ።
ቢቢሲ አማርኛ በቲክቶክ
አስተማማኝ ዜና እና መረጃን ቅድሚያ ለማግኘት ቢቢሲ አማርኛን ቲክቶክ ላይ ይከተሉ
የቢቢሲ አማርኛ ዩቲዩብ ቪድዮዎች
ቪዲዮ, ግብፅ ትቀላቀለዋለች እየተባለ ያለው ቱርክ፣ ሳዑዲ እና ፓኪስታን የመሠረቱት 'የሙስሊም ኔቶ'
ቱርክ፣ ሳዑዲ አረቢያ እና ፓኪስታን 'የመካ ስምምነት'ን ከፈረሙ ከአንድ ሳምንት በላይ ሆኗቸዋል። አንዳንድ ተንታኞች አገራቱ የተፈራረሙትን የመከላከያ ስምምነት "የሱኒ ስምምነት" ወይም "የሙስሊም ኔቶ" ሲሉ ጠርተውታል። አንዳንዶች እንደ ኢራን እና እስራኤል ላሉ አገራት የተላለፈ መልዕክት አድርገው አቅርበውታል። ሌሎች ደግሞ ይህ ስምምነት አገራቱ ለደኅንነት ዋስትና በዩናይትድ ስቴትስ ላይ ያላቸውን ጥገኝነት ለመቀነስ ያላቸውን ፍላጎት የሚያንፀባርቅ ነው ይላሉ። ነገር ግን ሙሉው ስምምነት ለሕዝብ ይፋ ባለመሆኑ እየተሰሙ ያሉት መላምቶች ብቻ ናቸው።
ቪዲዮ, “ጦርነት ከተጀመረ መንግሥታት ይለወጣሉ፤ ድንበሮች ይቀየራሉ”
ቢቢሲ በኢትዮጵያ እና በቀጣናዊ ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ በኬንያ የኢትዮጵያ አምባሳደር ባጫ ደበሌ ጋር ቃለ መጠይቅ አድርጓል። የኢትዮጵያ አሁናዊ ሁኔታ፣ ከህወሓት ጋር ያለው ውዝግብ፣ የባሕር በር ጥያቄ እና የቀጠናዊ የጦርነት ስጋቶች በቃለ መጠይቁ ተዳሰዋል። በተለይም በአፍሪካ ቀንድ ቀጣናዊ ጦርነት ከተጀመረ ውጤቱ መሠረታዊ ለውጥን የሚያስከትል ሊሆን እንደሚችል ተናግረዋል።
ቪዲዮ, ኢትዮጵያዊው የማይክሮሶፍት ባለሙያ ስለኤአይ ጥቅም እና ጉዳት ምን ይላሉ?
ዓለማችንን በማይታመን ፍጥነት እየለወጠ ያለውን ሰው ሠራሽ አስተውሎት (ኤአይ) በአግባቡ መገንዘብ ምርጫ ሳይሆን ግዴታ እየሆነ የመጣ ይመስላል። ስለ ሰው ሠራሽ አስተውሎት የተዛቡ ምልከታዎች ምንድን ናቸው? ለወደፊቱ የኤአይ ዓለም እንዴት እራሳችንን ማዘጋጀት እንችላለን? የሚሉና ተያያዥ ጥያቄዎችን በተመለከተ ኢትዮጵያዊው የማይክሮሶፍት ባለሙያ ዶ/ር ግርማው አበበ ታደሰ ምላሽ ሰጥቷል።
የቢቢሲ አማርኛ ዩቲዩብ ቻናልን ይቀላቀሉ
አነጋጋሪ ጉዳይ
በአዲስ አበባ ጉዳይ ላይ የክልል ፕሬዝደንቶች ሰጡ የተባለው አስተያየት እና የጎላው ልዩነት
ወደ ማጠናቀቂያው በተቃረበው የአገራዊ ምክክር ጉባኤ ላይ የአዲስ አበባ ጉዳይ መግባባት ያልተደረሰበት እና ሂደቱን ያዘገየ አጀንዳ ሆኗል። ሐሙስ ዕለት በተካሄደው ጉባኤ ላይ አዲስ አበባን በተመለከተ ክልል ርዕሳነ መስተዳድሮች ስለተነሱት ምክረ ሀሳቦች ምንጮች ለቢቢሲ ተናግረዋል። የኦሮሚያ እና አማራ ክልሎች አመራሮች መካከል በመዲናዋ ጉዳይ ልዩነት መታየቱንም ተሳታፊዎቹ ገልጸዋል።
ኢትዮጵያውያንን የሚመለከቱ አራት የፕሬዝዳንት ትራምፕ የኢሚግሬሽን ውሳኔዎች
ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ሁለት ዓመት ሊሞላው ወራት በቀረው የሁለተኛው የሥልጣን ዘመናቸው፣ ስደተኞች እና ጥገኝነት ጠያቂዎችን ዒላማ ያደረጉ ትዕዛዞችን አሳልፈዋል። በተለያየ መንገድ ኢትዮጵያውያን ላይ ጫና ሊያሳድሩ የሚችሉ የትራምፕ አስተዳደር አራት ውሳኔዎችን እንመልከት።
የግብፅ የኒውክሌር ኃይል ማመንጫ ግንባታ ላይ ተገኝቷል የተባለው ጉድለት እና ያስነሳው ውዝግብ
የግብፅ መንግሥት፣ በአገሪቱ የሚገነባው 'ኤል ዳባ' የኒውክሌር ኃይል ማመንጫ ማብላያዎች (ሪአክተር) ላይ "ጉድለት" እንደተገኘ በመግለፅ ግንባታውን የሚያከናውነው የሩሲያው ኩባንያ ላይ አቅርቦታል የተባለው ወቀሳ ውዝግብ አስነስቷል። “የኒውክሌር ደኅንነት አሠራር" ላይ ጥሰት ስለመፈጸሙ የወጣውን ዘገባ ተከትሎ ምላሽ የሰጡት የግብፅ ባለሥልጣናት፣ ጉዳዩን አስተባብለዋል።
አዲስ አበባ "የኦሮሚያ ክልል መቀመጫነቷ በሕገ መንግሥት እንዲደነገግ" ምክረ ሀሳብ ቀረበ
በኢትዮጵያ አገራዊ ምክክር ጉባኤ ሲከራክር በቆየው የአዲስ አበባ ጉዳይ ላይ የከተማዋ "የኦሮሚያ ክልል መቀመጫነት በፌደራል ሕግ መንግሥት እንዲሰፍር" የሚጠይቅ ምክረ ሃሳብ መቅረቡን ምንጮች ለቢቢሲ ተናገሩ። ከተማዋ "ከኦሮሚያ ክልል ጋር የሚኖራትን ግንኙነት" በተመለከተ ግን ኮሚሽኑ የመጨረሻውን የሚለው ምክረ ሀሳብ ለመንግሥት እንደሚያቀርብ ማስታወቁን አንድ ምንጭ ገልጸዋል።
በድሬዳዋ ከተማ ጉዳይ ላይ በሀገራዊ ምክክሩ ከምን ስምምነት ላይ ተደረሰ?
በሀገራዊው ምክክር ላይ የድሬዳዋ ከተማ በፌዴራል ከተሞች ጉዳይ ስር ምክክር ከተደረገባቸው ሁለት ከተሞች አንዱ ነው። ከኦሮሚያ እና ከሶማሌ ክልሎች በተወከሉ የምክክሩ አባላት መካከል ከፍተኛ የይገባኛል ክርክር እንደተደረገባት በምክክሩ ላይ የተሳተፉ ታማኝ ምንጭ ለቢቢሲ ተናግረዋል። ይሁን እንጂ የአዲስ አበባ ከተማ ጉዳይ ሰፊ መነጋገሪያ መሆኑ፣ የድሬዳዋ ጉዳይ ብዙም ትኩረት እንዳያገኝ አድርጎታል። ለመሆኑ በድሬዳዋ ላይ ምን ዓይነት ስምምነት ተደረሰ?
የአዲስ አበባን ጉዳይ ቅርቃር ውስጥ ያስገባው "ከበላይ የመጣ" ሃሳብ እና የምክክር ኮሚሽኑ ምላሽ
አንድ ወር ባስቆጠረው አገራዊ ምክክር ስምንት አጀንዳዎች ላይ ሲመክሩ የቆዩት ከአራት ሺህ በላይ ተሳታፊዎች ወደ መቋጫው እየተቃረቡ ነው። በዚህ ሂደት የአዲስ አበባ ጉዳይ ከሌሎች አጀንዳዎች በበለጠ አነጋጋሪ እና ስምምነት ላይ ለመድረስ አዳጋች ሆኖ ታይቷል። በአዲስ አበባ የምክክር አጀንዳ ላይ የተከሰተው ምንድን ነው? ያላግባቡት ጉዳዮችስ የትኞቹ ናቸው?
እስከ ግማሽ ሚሊዮን ብር የሚወጣባቸው ግዙፍ የሽምግልና አበባዎች፡ የአበባ አብዮት ወይስ የባህል ለውጥ?
ከጋብቻ በፊት የሚደረገው የሽምግልና ሥነ ሥርዓት ከፍተኛ ድግስ እና ገንዘብ የሚፈስበት እየሆነ መጥቷል። ከሚዘጋጀው ድል ያለ ድግስ ባሻገር በመቶ ሺዎች ብር የሚያስወጡ ቄንጠኛ ግዙፍ የአበባ ‘እቅፎች’ ደግሞ የሽምግልናው ሥርዓት አካል ሆነዋል። በተለይ የሚቀርበው የአበባ ስጦታ መነጋገሪያ ሆኗል። የሽምግልና ሥነ ሥርዓት የሰርግን ቦታ እየተካ ነው? ግዙፉ የአበባ ስጦታስ ከየት የመጣ ልማድ ነው?
አብን የሀገራዊ ምክክር ሂደት ላይ "መዋቅራዊ ጥሰቶች" እና "አንድ ወገን ብቻውን የሚወስንበት እንቅስቃሴ" ታይቷል ሲል ከሰሰ
የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን)፣ በሀገራዊ ምክክር ሂደት ላይ "ከተራ የአሠራር ግድፈት" የዘለሉ "ተደጋጋሚ እና የተደራጁ ጥፋቶች ተፈጽመዋል" ሲል ከሰሰ። "ገዢው አካል መዋቅራዊ ጥሰቶችን" እንደፈጸመ በማንሳት የከሰሰው አብን፣ በአዲስ አበባ ጉዳይ ላይ "የከተማዋ ነዋሪዎች ድምፅ እና ፍላጎት በአግባቡ ሳይወከል" መታለፉን ገልጿል። በሂደቱ ላይ የተፈጸሙት "ተደጋጋሚ እና የተደራጁ ጥፋቶች" የሀገራዊ ምክክሩን "ተዓማኒነት፣ አካታችነት፣ ገለልተኝነት እና ፍትሐዊነት ጥያቄ ውስጥ የሚስገቡ" እንደሆኑም ገልጿል።
ከአማራ ክልል ቀውስ ጋር በተገናኘ በሽብር ለተከሰሱት የቀረበው የይቅርታ ሰነድ ምን አካቷል? ተከሳሾቹስ ምን ምላሽ ሰጡ?
በአማራ ክልል ከተከሰተው ቀውስ ጋር በተያያዘ በሽብር ለተከሰሱት ከሦስት መቶ በላይ ፖለቲከኞች፣ ጋዜጠኞች እና ሌሎች ግለሰቦች በይቅርታ እንዲለቀቁ ሂደት ላይ ይገኛሉ። ለሽብር ተከሳሾች የቀረበው የይቅርታ ሰነድ በክልሉ ለተፈፀሙ ግድያዎች እና ጉዳቶች ተከሳሾቹ ኃላፊነት እንዲወስዱ የሚጠይቅ መሆኑን ቢቢሲ የተመለከተው ሰነድ ያሳያል።
በመተከል ዞን ታጣቂዎች በፈፀሙት ጥቃት በርካታ ሰዎች መገደላቸውን እና መቁሰላቸውን ነዋሪዎች ተናገሩ
በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል፣ መተከል ዞን በታጣቂዎች በተፈፀመ ጥቃት በርካታ ሰዎች መገደላቸውን እና መቁሰላቸውን ነዋሪዎች ለቢቢሲ ተናገሩ። ጥቃቱ የተፈፀመው ማክሰኞ ነሐሴ 6/ 2018 ዓ. ም. ጠዋት 12 ሰዓት ላይ በዞኑ ዋና ከተማ ግልገል በለስ በሚገኙ ቤተ ክርስቲያናት እና መናኸሪያ ላይ መሆኑን ነዋሪዎች ተናግረዋል።
በተስፋ ማጣት እና በሞት መሀል፡ የአማራ ክልል ሦስት የጦርነት ዓመታት
በአማራ ክልል ላለፉት ሦስት ዓመታት በፋኖ ኃይሎች እና በመንግሥት መካከል የሚካሄደው ግጭት የበርካቶችን ሕይወት ቀጥፏል፤ ከፍተኛ ሰብኣዊ እና ምጣኔ ሃብታዊ ውድመትም አድርሷል። ቢቢሲ አማርኛ ያነጋገራቸው የክልሉ ነዋሪዎች ከፍርድ ውጭ ግድያዎችን ጨምሮ ንጹኃን እስር እና እንግልትን እያስተናገዱ መሆኑን ይናገራሉ። የትጥቅ ግጭቶችን የሚመዘግበው አክሌድ ከጥር እስከ ሐምሌ 2018 ዓ.ም. ድረስ ባለው ጊዜውስት ብቻ ከስምንት ሚሊዮን በላይ ሰዎች 'ለግጭት' ተጋልጠዋል ብሏል። ቢቢሲ በግጭቱ በቀጥታ የተጎዱ ነዋሪዎችን እንዲሁም ባለሙያዎችን አነጋግሮ ቀጣዩን ዘገባ አሰናድቷል።
"አዲስ አበባ እንደ እንግዳ ካልሆነ ከዚህ በኋላ ለመኖር የምመጣ አይመስለኝም"
የሥዕል እና የቅርጻ ቅርጽ ባለሙያ የሆነው ዮናስ መኳንንት፤ ተወልዶ ያደገባትን፣ የእንጀራ ገመዱ የነበረችውን አዲስ አበባን ጥሎ ገጠር ከገባ ከጥቂት ወራት በኋላ ሁለት ዓመት ይሞላዋል። "እኔ እዚህ ከመጣሁ ትልቅ እረፍት ነው የሚሰማኝ። በጣም ሰላማዊ ቦታ ነው፤ ምንም ዓይነት የመኪና ድምጽ የለም፣ የምትሰማው የእንስሳት ድምጽ ብቻ ነው" ይላል።
ቢቢሲ አማርኛን በዋትስአፕ ላይ ያግኙ
የመካከለኛው ምሥራቅ ጦርነት
ግብፅ ትቀላቀለዋለች እየተባለ ያለው ቱርክ፣ ሳዑዲ እና ፓኪስታን የመሠረቱት 'የሙስሊም ኔቶ'
ቱርክ፣ ሳዑዲ አረቢያ እና ፓኪስታን 'የመካ ስምምነት'ን ከፈረሙ ከአንድ ሳምንት በላይ ሆኗቸዋል። አንዳንድ ተንታኞች አገራቱ የተፈራረሙትን የመከላከያ ስምምነት "የሱኒ ስምምነት" ወይም "የሙስሊም ኔቶ" ሲሉ ጠርተውታል።
የተባበሩት አረብ ኤምሬቶችን ቀጣናዊ ፖሊሲ የለወጠው የኢራን ጦርነት
የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ከአሜሪካ እና ከእስራኤል ጋር ባላት ግንኙነት የተነሳ የኢራን ዋነኛ ዒላማ ከሆነች በኋላ በቀጣናው አገራት ላይ ያላት መተማመን እየቀነሰች ነው። ለፖለቲካ፣ ለምጣኔ ሃብት እና ሌሎች ፍላጎቷን ለማሟላት ከቀጣናው ውጭ መመልከትን መርጣለች። ለዚህም ከሕንድ፣ ከዩክሬን፣ ከግሪክ፣ ከቆጵሮስ እና ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ትስስር እያጠናከረች ነው።
በሆርሙዝ ወሽመጥ ላይ የአሜሪካንን ባሕር ኃይል እየፈተኑ ያሉት የኢራን ትናንሽ ጀልባዎች
ፕሬዝዳንት ትራምፕ የኢራንን ባሕር ኃይል እንዳወደሙ ቢናገሩም፣ ኢራን ትናንሽ ፈጣን ጀልባዎችን በመጠቀም በሆርሙዝ ወሽመጥ የመርከቦችን እንቅስቃሴን መግታት ችላለች። ስለእነዚህ ውጤታማ የኢራን ፈጣን ወታደራዊ ጀልባዎች ምን እናውያለን?
የኢንተርኔት ዳታን በመቆጠብ የቢቢሲ አማርኛ ድረ ገጽን በቀላሉ ማንበብ ይፈልጋሉ?
የቢቢሲ አማርኛን ድረ ገጽ በቀላሉ በመክፈት ዜና እና ታሪኮችን በጽሑፍ ብቻ ያንብቡ!
ከየፈርጁ
ባለ ፓስፖርት አይጦች እና ስለ ቲቢ የሚመራመሩት ኢትዮጵያዊ
አይጦች በጎ ስም የላቸውም፤ ሰዎች ከቤታቸው፣ ምግብ እና የተለያዩ እቃዎች ከሚያስቀምጡባቸው ሥፍራዎች አይጦችን ለማራቅ መርዝ ወይም መጥመድ ይጠቀማሉ። በአጠቃላይ አይጦች ከጥፋት ጋር ስለሚያያዙ በበርካቶች ዘንድ የተጠሉ ናቸው። ኢትዮጵያዊው ሳይንቲስት ምርምር የሚያደርጉባቸው ባለ ፓስፖርት አይጦች ግን ለሰው ልጅ ጤና እና ደኅንነት ከፍተኛ ጥቅም አላቸው።
"አዳም አንድ ደራሲ የሚያስፈልጉት ሁሉም ግብዓቶች ተሟልተው ያሉት ፀሐፊ ነው"
የአዳም ረታ አዲሱ 'መዝሙረ ሄላም' የተሰኘው የረዥም ልብ ወለድ መጽሐፍ 1,008 ገጾች ሲኖሩት በአምስት ክፍሎች የተከፈለ ነው። ይህ የአዳም አዲስ መጽሐፍ ከዚህ ቀደም የሚጠቀማቸው እንደ ሕፅናዊነት ያሉ ሥነ ጽሑፋዊ ቴክኒኮችን የያዘ መሆኑን በመጽሐፉ አርትኦት ላይ የተሳተፈው ቢኒያም አቡራ ለቢቢሲ ተናግሯል። የመጽሐፉ መቼት ከዚህ ቀደም እንደነበሩ የደራሲው ሥራዎች ከ1950ዎቹ ማለቂያ እስከ 70ዎቹ መጨረሻ ያሉ ናቸው። መጽሐፉ መጠሪያ የሆነችው ሄላም ከዋና ገጸባሕሪያቱ አንዷ ስትሆን በሁሉም ክፍል ውስጥ ትገኛለች። ለሕፅናዊነት አጻጻፉ ኹነኛ ማስተሳሰሪያ በመሆን ታገለግላለች። ቢቢሲ ከአርታኢው ቢኒያም ጋር ያደረገውን ቆይታ እነሆ. . .
ሙዚቃ በሱቅ፣ በወጥ ቤት፣ በወፍጮ ቤት፣ በጋራዥ. . . የሚያጫውቱት ዲጄዎች
ዲጄ ሲባል መጀመሪያ የሚመጣልን ምሥል ምናልባትም የዳንስ ወለል ላይ ወዝ ወዝ የሚሉ ሰዎች እና ብልጭ ድርግም የሚል መብራት ይሆናል። እነዚህ ዲጄዎች ግን ማንኛውንም ቦታ ለሙዚቃቸው መዳረሻ ማድረግ የሚችሉ ናቸው። ጋራዥ፣ ቴአትር ቤት፣ ፀጉር ቤት፣ መጻሕፍት መደብር፣ ልብስ ሰፊ ቤት፣ ግንባታው ያልተጠናቀቀ 40/60፣ ሸክላ ሠሪ ቤት፣ ወፍጮ ቤት፣ ውይይት ታክሲ. . . የማይገቡበት የለም።
አጃኢብ!
በኢትዮጵያ 55 በመቶ ሴቶች ሚስትን ለመደብደብ የሚያበቃ ምክንያት አለ ብለው እንደሚያስቡ ጥናት አሳየ
በኢትዮጵያ ከግማሽ በላይ የሚሆኑ ሴቶች ባል ሚስቱን ለመደብደብ አሳማኝ ምክንያት ይኖረዋል ብለው እንደሚያምኑ የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ያደረገው ጥናት አመለከተ። ሚስትን ለመምታት አሳማኝ ምክንያት እንዳለ የሚያስቡ ወንዶች ብዛት ከሴቶች ያነሰ ቢሆንም፤ ከዚህ ቀደም ከነበረው አንጻር በ11 በመቶ ጨምሮ ተገኝቷል።
የተመለሱ ጥያቄዎች
በአፍንጫ በሚገባ ውሃ አማካኝነት የሚከሰተው አንጎልን የሚያጠቃው አስፈሪው ተህዋስ
ባለፈው ዓመት በሕንድ በዚህ አንጎልን በሚያጠቃ ጥገኛ ተህዋስ የተያዙ ከ200 በላይ ሰዎች ተመዝገበዋል። ይህ ቁጥር በዓለም በአንድ አገር የተመዘገበው ከፍተኛው ሲሆን ከቅርብ ወራት ወዲህ በአገሪቱ እንዲህ ዓይነት ኬዞች መታየታቸውን ቀጥለዋል። ከዚህ በፊት በዓለም አቀፍ ደረጃ የተመዘገቡ የበሽታው ክስተቶች ከ500 ያነሱ ነበሩ።



































































































