ከትራምፕ ጋር ሲጸልዩ የታዩት ጳጳሳት ከፕሬዝዳንቱ ጋር መገናኘታቸው "እንደጸጸታቸው" ተናገሩ

ከቀናት በፊት የተነሱት ፎቶዎች እና ቪድዮዎች፣ ጳጳሳቱ ትራምፕን ከብበው ሲጸልዩ ያሳያሉ
የምስሉ መግለጫ, ከቀናት በፊት የተነሱት ፎቶዎች እና ቪድዮዎች፣ ጳጳሳቱ ትራምፕን ከብበው ሲጸልዩ ያሳያሉ
ታትሟል
የንባብ ጊዜ: 2 ደቂቃ

የካቶሊክ ጳጳሳት ከዶናልድ ትራምፕ ጋር ሲጸልዩ የሚያሳይ ምሥል መውጣቱን ተከትሎ ከጳጳሳቱ ሁለቱ በዋይት ሀውስ ከፕሬዝዳንቱ ጋር መገናኘታቸው እንደጸጸታቸው ተናግረዋል።

ጳጳሳቱ ከትራምፕ ጋር ሲጸልዩ የሚያሳየው ምሥል እንደ ፖለቲካዊ አቋም መወሰዱን ተከትሎ ጳጳሳቱ ከትራምፕ ጋር በመገናኘታቸው እንደተጸጸቱ አስታውቀዋል።

ከቀናት በፊት የተነሱት ፎቶዎች እና ቪድዮዎች፣ ጳጳሳቱ ትራምፕን ከብበው ሲጸልዩ ያሳያሉ።

የሚልዋኪ ሊቀ ጳጳስ ጄፍሪ ግሮብ እንዳሉት እንደተናገሩት፣ ከፕሬዝዳንቱ ጋር የተገናኙት በግል ቢሆንም ምሥሉ "ለፖለቲካ መጠቀሚያ" ውሏል።

ትራምፕ እና የካቶሊክ ሊቀ ጳጳስ ሊዮ ያላቸው ግንኙነት ከሻከረ ሰነባብቷል። የተወሰኑ የአሜሪካ ጳጳሳትም ትራምፕ በስደተኞች ላይ የያዙትን አቋም ተችተዋል።

ትራምፕ በ2024 ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ 55 በመቶ የካቶሊኮችን ድምጽ ማግኘታቸውን ጥናቶች ያሳያሉ።

የአዮዋ ጳጳስ ዊልያም ጆንሰን እንዳሉት ከትራምፕ ጋር የተገናኙት በዋይት ሀውስ የእምነት ጉዳዩች ክፍል አማካኝነት ነው።

ስደትን፣ ዓለም አቀፍ የጳጳሳት ቪዛን እና አቅም ደካሞች ላይ የሚደርሰውን ብዝበዛ በተመለከተ ውይይት እንደሚካሄድ ተገልጾላቸዋል።

Skip podcast promotion and continue reading
BBC News Amharic የቢቢሲ አማርኛ ዩቲዩብ ቻናላችንን ይቀላቀሉ!
የቢቢሲ አማርኛ ዩቲዩብ ቻናል

ዜና፣ ትንታኔ እና ታሪኮችን በምሥል እና በድምጽ ለማግኘት

ይህንን በመጫን ሰብስክራይብ ያድርጉ

End of podcast promotion

"ማንኛችንም ብንሆን የትኛውንም የፖለቲካ ፓርቲ ወይም እጩ ለመደገፍ አልተገኘንም" ብለዋል።

ከፕሬዝዳንቱ ጋር መገናኘታቸው ወደ ፖለቲካዊ አጀንዳ መለወጡን "መሰሪነት" ሲሉ ኮንነዋል።

የፕሬዝዳንቱ የኮምንኬሽን አማካሪ ማርጎ ማርቲን ከጳጳሳቱ ጋር የነበረውን ቆይታ የሚያሳይ ቪድዮ አጋርተዋል።

ሊቀ ጳጳስ ጄፍሪ ግሮብ እንደተናገሩት ጳጳሳቱ ለ90 ደቂቃ ያህል ከባለሥልጣናት ጋር ከተወያዩ በኋላ ወደ ትራምፕ ጽሕፈት ቤት ተወስደዋል።

ከትራምፕ ጋር የተነሱት ፎቶ ከሌሎች የሃይማኖት መሪዎች ጥያቄ እንዳስነሳ ተናግረዋል።

"ከምርጫው ከሁለት ሳምንት በፊት ሳላስበው በፖለቲካዊ ክንውን እንደተሳተፍኩ የሚገልጹ መልዕክቶች ይደርሱኝ ጀመር" ብለዋል።

በፕሬዝዳንቱ ፖሊሲ ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎችም "ማዘናቸውን" እንደገለጹ ተናግረዋል።

ቢቢሲ ስለ ጉዳዩ ለዋይት ሀውስ ጥያቄ ቢያቀርብም የተሰጠው ምላሽ በቀጥታ የጳጳሳቱን ቅሬታ ወይም ከትራምፕ ጋር መገናኘቸውን የተመለከተ አይደለም።

የዋይት ሀውስ ቃል አቀባይ ቴይለር ሮጀርስ "ለካቶሊክ አሜሪካውያን ከትራምፕ የበለጠ ፕሬዝዳንት ኖሮ አያውቅም" ብለዋል።

በአሜሪካ የሃይማኖት ጉዳዩች ላይ ጥናት የሚሠራው 'ፒው' ተቋም እንደገለጸው፤ ዋነኛ የሃይማኖት ተቋማት ለትራምፕ የሚሰጡት ድጋፍ ቀንሷል።

ትራምፕ ሥልጣን ሲይዙ የነራቸው የካቶሊኮች ድጋፍ 47% የነበረ ሲሆን አሁን ላይ ወደ 30% ወርዷል።

የአሜሪካ አጋማሽ ዘመን ምርጫ ኮንግረስን የሚቆጣጠረውን ፓርቲ ይወስናል።

42 በመቶ ካቶሊኮች ዴሞክራቶች የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትን በአብላጫ እንዲይዙ ሲፈልጉ፤ 39 በመቶዎቹ ደግሞ ለሪፐብሊካኖች ድጋፍ አሳይተዋል።

ትራምፕ ስደተኞችን ከአሜሪካ ከማባረራቸው ጋር በተያያዘ ከሊቀ ጳጳስ ሊዮ ጋር በተደጋጋሚ ተጋጭተዋል።

የካቶሊክ ጳጳሳት ከትራምፕ ጋር ከመገናኘታቸው ከቀናት በፊት ሊቀ ጳጳስ ብሬንደን ቻሂል እና የአሜሪካ ብሔራዊ ኢቫንጃሊካል ማኅበር ፕሬዝዳንት ዋልተር ኪም ባወጡት መግለጫ "ስደተኞችን የተመለከተ ክርክር ክስቲያናዊ ርህራሄ እና ብልሀት የተሞላው" እንዲሆን አሳስበዋል።

ስደተኞች ላይ የሚወሰደው እርምጃ "ፍርሃት የፈጠረ፣ ቤተሰቦችን የነጣጠለ፣ ሕጋዊ ሒደትን ያልተከተለ እና ጎረቤቶቻችንን ያንቋሸሸ ነው" ሲሉም ኮንነዋል።

በቅርቡ የትራምፕ አስተዳደር ወታደራዊ የሞት ቅጣትን በቀጥታ ለማስተላለፍ ይዞት የነበረው ዕቅድ በካቶሊክ ሊቀ ጳጳሳት ጣልቃ ገብነት መሰረዙ ይታወሳል።